ከጓደኞቿ ውስጥ በሞገደኝነት የምትታወቀው ፍቅር በራሳ የምትተማመን እና ሃሳቧን በነፃነት ለመግለፅ ወደሃላ የማትል ልጅ ነች። ፍቅር ስለአካባቢዋ አና በዙሪያዋ ስላሉ ሰዎች ማሰብ አና መረዳት ያስደስታታል።
ፍቅር የምትኖረው ገጠር ቀመስ ከሆኑት ወላጆቿ፥ ከታናሽ እህቷ ጋር እና ከአክስቷ ልጅ ጋር ነው። ፍቅር ለታናሽ አህቷ ሳባ ትልቅ ሃላፊነት ይሰማታል።
ፍቅር የየኛ ባንድ ዋና ቁልፍ አባል ስትሆን የግጥም እና የስነፅሁፍ ፍላጎት አላት። የባንዱንም የሙዚቃ ግጥም የምትፅፈው ፍቅር ራሳ ናት።
ፍቅር አንዳንዴ ከስርዓቶች ጋር አና ከበላዮቿ ጋር ባለመግባባት ግጭት ውስጥ ትገባለች። ፍቅር በባህሪዋ ቀጥተኛ ስለሆነች ብዙዎች ይህን አንደ ድፍረት ይመለከቱባታል። ፍቅር ሃሳቧን ሳትፈራ በመግለፅ ብትታወቅም ግን ልብ የሚሰብር ሚስጥር ደብቃ ይዛለች፡፡