መልካም እና ቅን አለም ለተገፉ የምትቆም፥ ከባድ የሚመስሉ ነገሮች ውስጥ እጃን ማስገባት የምትወድ እና የፈጠራ ክንውኖች የሚያስደስታት ልጅ ነች።
አለም ህልሟን ማሳካት ለሳ ትልቅ ቦታ ያለው ሲሆን ከህልሞቿ መሃል ሙዚቀኛ መሆን በመጀመሪያ ደረጃ ታስቀምጠዋለች። ነገር ግን አለም ህልሟን ለማሳካት ካላት ጉጉት የተነሳ በምትሄደው ርቀት ራሷን ችግር ውስጥ ገብታ ታገኘዋለች።
የአለም ቤተሰቦች ጥሩ ገቢ ያላቸው ሲሆኑ በሚኖሩበት ከተማ ውስጥ ያቋቋሙትን ሆቴል በማስተዳደር ይተዳደራሉ። አለም በአባቷ ተንቀባራ ያደገች በመሆና አልፎ አልፎ በምታሳየው ፀባይ ከእናቷ ጋር ትጋጫለች።
አለም ከወንድሟ ዳዊት ጋር ጥሩ የሚባል ግንኙነት ቢኖራትም ከአንድ አጋጣሚ በኋላ ስለወንድሟ ያላትን አመለካከት አሉታዊ በሆነ መልኩ ቀይሮታል።
አለም በግዋደኛዋ ፍቅር በጣም የምትወደድ ሲሆን ከፍቅር እና ከሌሎች ጓደኞቿ ጋር በመሆን የሙዚቃ ባንድ እንዲቋቋም የሚል ሃሳብ አፍልቃለች።
የአለም ህይወት ከውጪ ሲታይ ሁሉ የሞላላት ቢመስልም የቤት ውስጥ አውነታዋ ግን ከዚህ አጅግ የራቀ ነው።